BBC News, አማርኛ - ዜና
ዜና
ቀጥታ, አሜሪካ ወሳኝ የጦር አውሮፕላኖችን ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ማሰማራቷ ተረጋገጠ
የአሜሪካ ከፍተኛ የብሔራዊ ደኅንነት ባለሥልጣናት ለፕሬዝዳንት ትራምፕ የአገሪቱ ጦር ኢራን ላይ ሊፈጸመው ስለሚችለው ጥቃት ምክር ማቅረባቸው ከተሰማ በኋላ፣ የቢቢሲ መረጃ ማጣሪያ ክፍል የተለያዩ መረጃዎችን በመጠቀም ባደረገው ማጣራት ወሳኝ የሆኑ የአሜሪካ የጦር ጄቶች በባሕረ ሰላጤው አካባቢ መሰማራታቸውን አረጋገጠ።
ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል በሚል ስጋት ውስጥ መኖር
ግጭቶች በሰው ሕይወት እና አካል እንዲሁም በንብረት እና በመሠረተ ልማቶች ላይ ከሚያደርሱት ጉዳት ባሻገር በሰዎች አካላዊ እና ሥነ ልቦናዊ ጤና እና ደኅንነት ላይ ከባድ ተጽእኖን እንደሚያስከትል ባለሙያዎች ይናገራሉ። እንዲህ ባለው ሁኔታ ውስጥ ስንሆን የሚከሰቱ ሥነ ልቦናዊ ለውጦች ምንድን ናቸው? ለመቋቋምስ ምን ማድረግ እንችላለን?
"የአፍሪካ ቀንድ የውጭ ኃይሎች የጦር ሜዳ መሆን የለበትም" - የቱርክ ፕሬዝዳንት ኤርዶዋን
ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡት የቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን አገራቸው በአፍሪካ ቀንድ "አዲስ ግጭቶች እና ሕመም መመልከት" እንደማትፈልግ እንዲሁም ቀጣናው "የውጭ ኃይሎች የጦር ሜዳ" መሆን እንደሌለበት ተናገሩ። የቱርኩ ፕሬዝዳንት አክለውም፤ እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችው የአገርነት ዕውቅና "ለሶማሊላንድም ሆነ ለአፍሪካ ቀንድ ምንም ጥቅም" አይኖረውም ብለዋል።
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናልን ይቀላቀሉ
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቪድዮዎች
ቪዲዮ, ቱርክን ወደ ኦቶማን ዘመን ዝናዋ ለመመለስ የሚጥሩት ኤርዶዋን ምን እያደረጉ ነው?
ቱርክ ከኦቶማን ግዛተ መንግሥት መውደቅ በኋላ እንደ አገረ መንግሥት ከተመሠረተች 100 ዓመታት አለፋት። የቱርክ አባት በመባል የሚታወቁት አታቱርክ፣ አገራቸውን ከሃይማኖት ገለልተኛ እና ዘመናዊ እሳቤን እንድትላበስ መሠረት ጥለዋል። በዘመናዊው ዓለም መድረክ ጉልህ ተጽዕኖ ያላቸው የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶዋን እንደ ኦቶማን ዘመን ሁሉ ቱርክን በዓለም ኃያል ለማድረግ እየጣሩ ነው። ይሳካላቸው ይሆን?
ቪዲዮ, ኢትዮጵያ የባሕር በር “በባሌም ሆነ በቦሌ ማግኘቷ አይቀርም”- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር መንግሥታቸው ከኤርትራ ጋር ስለገባበት ቅራኔ አጀማመር ከዚህ በፊት ያልተናገሩትን ጉዳይ እማኞችን ጠቅሰው ተናግረዋል። በተጨማሪም በሁለቱ አገራት መካከል ለተፈጠረው መቃቃር ሌላ ምክንያት የሆነው የኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ፍላጎት “በባሌም ሆነ በቦሌ” የሚሳካ ነው በማለት በአርግጠኝነት ነው ተናግረዋል።
ቪዲዮ, ፕሬዝዳንት ትራምፕ ስለሕዳሴ ግድብ እስካሁን ምን አሉ?
ከቀናት በፊት በአባይ (ናይል) ጉዳይ ኢትዮጵያ እና ግብፅን ለማደራደር ጥያቄ ያቀረቡት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ኢትዮጵያ የናይል ወንዝ "ፍሰትን የሚያስቆም ግድብ" ሠርታለች አሉ። በዚህም ምክንያት ግብፅ ከናይል ወንዝ "በቂ ውሃ እንደማታገኝ" የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ፤ ይህንን ጉዳይ "መፍታት ይኖርብኛል" ሲሉ ተደምጠዋል። ለመሆኑ ፕሬዝዳንቱ በተለያዩ ወቅቶች በጉዳዩ ዙሪያ ምን ተናገሩ?
ቪዲዮ, የቢሾፍቱ አየር ማረፊያ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ምን ማለት ይሆን?
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ አቅራቢያ 'አቡሴራ' በተባለ አካባቢ የሚገነባው አዲስ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ቅዳሜ ጥር 2/2018 ዓ.ም. መሠረተ ድንጋይ ተቀምጧል። 12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር የሚወጣበት የአውሮፕላን ማረፊያ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ሲጠናቀቅ፣ በዓመት 60 ሚሊዮን መንገደኞችን ማስተናገድ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል። 3,500 ሔክታር መሬት የሚሸፍነው ይህ ግዙፍ የአውሮፕላን ማረፊያ አውሮፕላን ማረፊያ በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባ በዓመት 110 ሚሊዮን መንገደኞችን ያስተናግዳል ተብሏል።
ቪዲዮ, ከፍተኛ የነዳጅ ሀብት ያላት አሜሪካ ለምንድን ነው በሌሎች አገራት ነዳጅ ላይ ዐይኗን የጣለችው?
አሜሪካ ከፍተኛ የነዳጅ ክምችት ቢኖረትም በሌሎች አገራት ውስጥ ባሉ የነዳጅ ክምችቶች ላይ ዘወትር ትረኩት ደታርጋለች። ለዚህ በበርካታ አገሮች ጦርነት ውስጥ በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ ስትሳተፍ ቆይታለች። በቅርቡም በቬንዙዌላ ሰጥ ቀጥተኛ ወታደራዊ እርምጃ በመውሰድ መሪዋን ይዛ ወስዳለች። ከዚያም በኋላ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በቬንዙዌላ የነዳጅ ሀብት ላይ አሜሪካ ያላትን ፍላጎት በይፋ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ተደምጠዋል።
ቪዲዮ, “ጦርነትን በተግባር እናውቀዋለን” ፕሬዝዳንት ኢሳያስ
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከአገራቸው ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ላለው ውጥረት እና ለተፈጠረው ችግር ከጀርባ ሆኖ የሚገፋ ወገን እንዳለ ተናግረዋል። ጦርነት ሊከሰት የሚችልበት እድል እንዳለ የጠቆሙት ፕሬዝዳንቱ ለዚህም ዝግጁ መሆናቸውን በመግለጽ “ጦርነትን በተግባር እናውቀዋለን” ብለዋል።
ቪዲዮ, አሜሪካ ዐይኗን የጣለችው በማዱሮ ላይ ወይስ በቬንዙዌላ ነዳጅ ላይ?
አሜሪካ ማዱሮ ላይ በዕጽ እና በጦር መሳሪያ ዝውውር ብትከሳቸውም ዋነኛ ትኩረቷ ቬንዙዌላ ባላት የተትረፈተፈ የነዳጅ ሀብት ላይ እንደሆነ ይነገራል። ትራምፕም ይህንን ሳይደብቁ ተገቢው ሽግግር እስኪደረግ ድረስ ቬንዙዌላ በአሜሪካ እንደምትመራ እና ኩባንያዎቿ የነዳጅ ምርት ሥራውን እንደሚረከቡ በግልጽ ተናግረዋል።
ቪዲዮ, የሶማሊላንድ ቀጣዩ ዕውቅና የማግኘት ፈተና፡ ቀጥሎ ማን ዕውቅና ይሰጣታል?
እስራኤል ለሶማሊላንድ አገርነት ይፋ ዕውቅና መስጠቷን ተከትሎ የሶማሊላንድ እና የሶማሊያ እንዲሁም የቀጣናው ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል የሚለው ጥያቄ መነሳት ጀምሯል።
ቪዲዮ, ይህ የኢትዮ ጃዝ ፈጣሪው ሙላቱ አስታጥቄ የመጨረሻ የሙዚቃ ሥራው ይሆን?
የሙላቱ የሙዚቃ ጉዞ አስርት ዓመታትን ያስቆጠረ ነው። የተወለደው በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያዋ ከተማ ጅማ ነው። ነገር ግን ለዩናይትድ ኪንግደም ትልቅ ቦታ አለው። ትምህርቱን በዌልስ ነው የተከታተለው። ሙላቱ ወደ ሙዚቃው ዓለም እንዴት ገባ? ከዚህ በኋላስ መድረክ ላይ እናየው ይሆን?
አነጋጋሪ ጉዳይ
"ተወዳጇ እና ደስተኛዋ ልጄ እንዴት በራሷ ላይ ወሰነች?" - በቲክ ቶክ እና በእኩዮቿ ጫና ራሷን ያጠፋቸው ኢትዮጵያዊት ታዳጊ
አቶ ነብዩ ማኅበራዊ ሚዲያ በታዳጊ ልጆች ላይ የሚያስከትለውን ተጽእኖ በተመለከተ መራራ የሆነ ልምድ ነው ያላቸው። የ13 ዓመቷ ልጃቸው ፊዮሬላ ላይ ምንም ዓይነት ምልክት ሳይመለከቱ በእኩዮቿ ጫና እና በማኅበራዊ ሚዲያ ግፊት ባላሰቡት ጊዜ ልጃቸው እራሷን አጥፍታ አግኝተዋታል።
ከሰሞኑ በደብረ ታቦር ከተማ የተከሰተው ምንድን ነው?
በአማራ ክልል የደቡብ ጎንደር ዞን መቀመጫ በሆነችው ደብረ ታቦር ከተማ በፋኖ ታጣቂዎች እና በመንግሥት ኃይሎች መካከል በተካሄደ ግጭት የሕይወት እና የንብረት ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎች ተናገሩ። የከተማዋ አስተዳደር ባወጣው መግለጫ ታጣቂዎች በመንግሥት እና በግለሰብ ንብረት ላይ ውድመት እና ዘረፋ መፈፀማቸውን አመልክቷል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ሆኖ በውጭ ምንዛሬ ክፍያ ለመፈጸም የሚያስችል ዓለም አቀፍ የክፍያ ካርድ ማግኘት ተፈቀደ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፤ የውጭ ምንዛሬ ሒሳብ (አካውንት) ያላቸው ደንበኞች የቪዛ እና የበረራ ትኬት ማቅረብ ሳይጠበቅባቸው ለዓለም አቀፍ የበይነ መረብ (ኦንላይን) ግብይቶች የሚውል የውጭ ምንዛሬ ክፍያ ካርድ እንዲያገኙ ፈቀደ። በተጨማሪም በአዲሱ መመሪያ መሠረት፤ ኢትዮጵያውያን "ከአገር ውጭ ለሚኖሩ ዘመዶቻቸው እገዛ" የሚውል እስከ 3,000 ዶላር የሚደርስ ገንዘብ ወደ ሌላ አገር መላክ ይችላሉ።
የኢትዮጵያ እና የኤርትራ 'የቃላት ጦርነት' ለምን አሁን ተካረረ? ወዴትስ ያመራል?
ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሲለዋወጡት የቆዩት 'የቃላት ጦርነት' ከመቼው በበለጠ አሁን ላይ መካረሩን የሚጠቁሙ ምልክቶች እየተስተዋሉ ይገኛሉ። ኢትዮጵያ "ኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት በመግባት የተወሰኑ አካባቢዎችን ተቆጣጥራለች" እንዲሁም "ታጣቂዎችን ትደግፋለች" ብላ ያቀረበችውን ክስ ኤርትራ "ሐሰተኛ እና የፈጠራ" ስትል አጣጥላለች። ለመሆኑ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ያለው 'የቃላት ጦርነት' አሁን ላይ እየተካረረ የመጣው በምን ምክንያት ነው? ወዴትስ ሊያመራ ይችላል?
ኤርትራ ሠራዊቷን በአስቸኳይ ከግዛቷ እንድታስወጣ እና ለድርድር ዝግጁ እንድትሆን ኢትዮጵያ ጠየቀች
የኤርትራ ሠራዊት ተቆጣጣሯቸዋል ካላቸው የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛቶች እንዲወጣ እና ለድርድር ዝግጁ እንዲሆን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጠየቀ። ሚኒስቴሩ ቅዳሜ ጥር 30/2018 ዓ.ም. ለኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ ላይ ኤርትራ የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ድንበር በመጣስ በሰሜን ምሥራቅ አቅጣጫ የሚገኙ አካባቢዎችን ተቆጣጥራ እንደምትገኝ ገልጿል።
ኤርትራ "ትርጉም የለሽ ውዝግብ ውስጥ ለመግባት ፍላጎት የለኝም" ስትል የኢትዮጵያን ክስ አጣጣለች
ኤርትራ የኢትዮጵያ ያቀረበችባትን ክስ "ትርጉም የለሽ" በማለት በዚህ ውዝግብ ውስጥ ለመግባት ፍላጎት እንደሌላት በማስታወቂያ ሚኒስቴሯ በኩል ባወጣችው አጭር መግለጫ አስታወቀች። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት በመግባት የተወሰኑ አካባቢዎችን ተቆጣጥራለች እንዲሁም ታጣቂዎችን ትደግፋለች ሲል ቅዳሜ ዕለት በጻፈው ደብዳቤ ክስ እና የድርድር ጥያቄ አቅርቦ ነበር።
የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን የፓርላማ ንግግር አስተባበሉ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በትግራይ ጦርነት ወቅት የኤርትራ ሠራዊት የሚፈጽማቸውን ግፎች እንዲያቆም የሚጠይቅ መልዕክት ወደ አሥመራ እንደላኩ የገለጹበትን የፓርላማ ንግግር የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው አስተባበሉ። በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተሠራጨው ባለሦስት ገጽ ደብዳቤም የራሳቸው መሆኑን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።
'በጥቁር ገበያ ነጋዴዎች' እጅ የወደቀው የትግራይ ክልል የነዳጅ አቅርቦት
የትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቀለን ጨምሮ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ከፍተኛ የነዳጅ አቅርቦት እጥረት ካጋጠመ ወራት መቆጠራቸውን ባለሥልጣናት እና የነዳጅ ማደያዎች ይናገራሉ። ነገር ግን ነዳጅ ከእጥፍ በላይ በሆነ ዋጋ በጥቁር ገበያ እየተሸጠ ይገኛል። ይህ ነዳጅ ከየት ነው የሚመጣ? የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ነው።
የኢንተርኔት ዳታን በመቆጠብ የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽን በቀላሉ ማንበብ ይፈልጋሉ?
የቢቢሲ አማርኛን ድረ ገጽ በቀላሉ በመክፈት ዜና እና ታሪኮችን በጽሑፍ ብቻ ያንብቡ!
ከየፈርጁ
የታዋቂ ሰዎችን ስም መነጋገሪያ ያደረገው የወሲብ ወንጀለኛው ጄፍሪ ኤፕስቲን ማን ነው?
የጄፍሪ ኤፕስቲን ሰነዶች ይፋ መሆናቸውን ተከትሎ በመላው ዓለም የሚገኙ ታዋቂ ግለሰቦች እና ተቋማት በአሉታዊ መልኩ ስማቸው እየተነሳ ነው። በዚህም ምክንያት ፖለቲከኞች እና ታዋቂ ሰዎች ዝናቸው ጥያቄ ውስጥ ገብቶ አንዳንዶቹም ከሥልጣን እና ከኃላፊነታቸው እየለቀቁ ነው። ለመሆኑ ለዚህ ሁሉ ቀውስ ምክንያት የሆነው ጄፍሪ ኤፕስቲን ማን ነው?
"ሊቢያ ውስጥ በርካታ ስቃይ ባሳልፍም፤ በአይኤስ የተቀጠፉትን ወንድሞቼን በፍጹም አልረሳም" ዳንኤል አብርሃ
ከ30 በላይ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን በሊቢያ በአይኤስአይኤስ ከተገደሉ 11 ዓመት ሆኖታል። ያንን አሰቃቂ ግድያ ተዓምር በሚመስል መልኩ የተረፈው ዳንኤል አብርሃ ከአዲስ አበባ -ሊቢያ ከዚያም ዩናይትድ ኪንግደም ያለፈበትን ሁኔታ ስለሚተርክበት መጽሐፉ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርጓል።
ቢቢሲ አማርኛን በዋትስአፕ ላይ ያግኙ
አጃኢብ!
"እናቴ መርዝ ልታበላኝ ስትል ደረስኩባት…" ሁላችንም ትንሽ ትንሽ 'እያበድን' ይሆን?
ስኪዞፍሪኒያ የሚባል የአእምሮ ጤና መታወክ እንዴት ያለ ነው? ፕሮፌሰር ሰለሞን ተፈራ ፒኤችዲ ሠርተውበታል። ለ20 ዓመት ተመራምረውበታል። በስኪዞፍሬኒያ የሚሰቃዩ በርካታ ታካሚዎች ነበሯቸው፤ አሏቸው። ፕሮፌሰሩ ነገርን በአጭር የማስረዳት ፀጋ አላቸው። ይህን የአእምሮ በሽታ እንዲህ ይገልጹታል። "ነገሩ የማርያምን ብቅል ሲፈጩ መዋል ነው" ይሉታል። ምን ማለታቸው ነው?
የእስራኤል እና የኢራን ግጭት
አደገኛው ታጣቂ ቡድን አይ ኤስ በምዕራቡ ዓለም ዳግም እየተጠናከረ ይሆን?
አይኤስ በመካከለኛው ምሥራቅ የነበረውን ድጋፍ እያጣ ከመጣ ወዲህ በአፍሪካ የተለያዩ አገራት ውስጥ እግሩን እያስገባ ነው። በምዕራብ አፍሪካ አገራት 12ሺህ የሚደርሱ ተዋጊዎች ያሉት አይኤስ በጎረቤት አገር ሶማሊያ ውስጥም ይንቀሳቀሳል። በዴሞክራቲክ ኮንጎ፣ በሞዛምቢክ እና ናይጄሪያም ቡድኑ እንቅስቃሴዎችን ያደርጋል።
በቀይ ባሕር የጦር ሰፈር ለማቋቋም የተቃረበችው ሩሲያ ለቀጣናው ምን ይዛ ትመጣለች?
ከከተፎካካሪዎቿ ዘግይታ ወደ ቀይ ባሕር ወታደራዊ ኃይሏን ለማስፈር የተቃረበችው ሩሲያ በወሳኙ የባሕር መተላለፊያ ላይ ላይ አዲስ ኃይል ትሆናለች። በአፍሪካ የመጀመሪያዋን የባሕር ኃይል ጦር ሰፈር ለመመሥረት ስትጥር የቆየችው ሩሲያ አሁን ፍላጎቷን ዕውን ለማድረግ ተቃርባለች። ይህ የሩሲያ ኃይል ወደ ቀጣናው መምጣት ምን ይዞ ይመጣል?
አሜሪካ የ10 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ያቀረበችበት የዋይት ሐውስ እንግዳ፡ አህመድ አል ሻራ
አዲሱ የሶሪያ ፕሬዝዳንት አህመድ አል ሻራ በአግባቡ የተተኮሰ ሱፍ ለብሰው፣ ፀጉራቸውን ወደ ኋላ አበጥረው ወደ ዓለም አቀፍ መድረክ ሲመጡ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንዳሉ ያስታውቃል። አሁን የትግል ልብሳቸውን ትተው፣ አዲስ ስም ይዘው በዓለም ላይ ካሉት በጣም ኃያላን መሪዎች ጋር ይጨባበጣሉ።
በመካከለኛው ምሥራቅ ኃያል የሆነችው የአይሁዶች አገር እስራኤል እንዴት ተመሠረተች?
በመካከለኛው ምሥራቅ ኃያል እና ብቸኛዋ የአይሁዶች አገር የሆነችው እስራኤል በዙሪያዋ ካሉ አገራት ሁሉ በዕድሜ ትንሿ ናት። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቃት በኋላ በአውሮፓውያኑ 1948 የእስራኤል እንደ አገር መመሥረት በአካባቢው አሁን ድረስ እየተካሄደ ያለ ለውጥን አስከትሏል። ለመሆኑ በየዕለቱ የዓለም መገናኛ ብዙኃን ስሟን ሳያነሱ የማያልፏት ይህች አገር እንዴት ተመሠረተች?
እስራኤል 15 የጦር አውሮፕላኖችን አሰማርታ ኳታር ውስጥ የፈጸመችው ጥቃት
በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ ውስጥ እስራኤል ጥቃት የፈጸመችው በርካታ የሐማስ ፖለቲካ ቢሮ ባለሥልጣናት በሚኖሩበት የመኖሪያ አካባቢ ላይ ነው። በዚህ ጥቃት አስከ ስምንት የሚደርሱ ፍንዳታዎችን እና ከፍተኛ ጭስ በዶሃ ሰሜናዊ ክፍል ላይ ማየታቸውን ዓይን እማኞች ተናግረዋል። ከጥቃቱ ደቂቃዎች በኋላ ደግሞ እስራኤል ለተፈጸመው ጥቃት በይፋ ኃላፊነቱን ወስዳለች።
የእስራኤል ፕሬዝዳንት እንዲሆን ተጠይቆ የነበረው ታዋቂው የፊዚክስ ሊቅ አልበርት አንስታይን
የጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ቤን ጉርዮን መንግሥት በዓለም ታዋቂ የሆነው ሳይንቲስት አልበርት አንስታይን ለእስራኤል ፕሬዝዳንትነት እንዲሆን ካጩት በኋላ በዩናይትድ ስቴትስ የእስራኤል አምባሳደር አባ ኢባን አንስታይንን እንዲያነጋግሩ ተደረገ።
የተመለሱ ጥያቄዎች
አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ ቢሾፍቱ እንዲሆን ለምን ተመረጠ?
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ግዙፍ የሚባለው የአውሮፕላን ማረፊያ ከአዲስ አበባ 40 ኪሎ ሜትር ያህል በሚርቅ ቦታ ላይ ለመገንባት ሥራ ጀምራለች። ይህ አውሮፕላን ማረፊያ መሃል አዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኘው በብዙ እጥፍ የሚበልጡ መንገደኞችን ያስተናግዳል ተብሏል። ይህንን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን ለምን አሁን መገንባት አስፈለገ? ቦታውስ ለምን ተመረጠ?
በሴቶች ላይ እየበረታ ከመጣው የማኅበራዊ ሚዲያ ጥቃት እንዴት ራስን መጠበቅ ይቻላል?
በዓለም አቀፍ ደረጃ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት እስከ 58 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች እና ልጃገረዶች በኦንላይን ለሚፈጸሙ ጥቃቶች ዒላማ መሆናቸውን የተባበሩት መንግሥታት የሴቶች ድርጅት አስታውቋል።
ሌላ ዕይታ
ቢቢሲ አማርኛን በማኅበራዊ ሚዲያዎች ይከታተሉ
ከማኅደራችን
ማርበርግ ቫይረስ: የመጀመሪያው ታማሚ እና ሦስት መሪዎቿን ያጣችው የጂንካ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን
ከሌሊት ወፎች የሚነሳው የማርበርግ ቫይረስ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ከተገኘ አንድ ወር ሊደፍን ጥቂት ቀናት ቀርተውታል። የጤና ሚኒስቴር፤ እንዴት በሽታው በጂንካ ከተማ ሊነሳ እንደቻለ እስካሁን አልገለጸም። ለመሆኑ በጂንካ የመጀመሪያው ታማሚ ማን ነበር? የበሽታው መነሻ የሆኑት የሌሊት ወፎችን እና የመጀመሪያውን ታማሚስ ምን አገናኛቸው? ቢቢሲ ባደረጋቸው በርካታ ቃለ መጠይቆች ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ የሚሆኑ መረጃዎች አሰባስቧል።
"ቢገድሉኝ ይሻል ነበር"፡ የሴቶችን ሕይወት እያበላሸ ያለው የተዘነጋው የአማራ ክልል ጦርነት
ከሁለት ዓመት በላይ የሆነው በአማራ ክልል በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በሚካሄደው ግጭት ሰላማዊ ሰዎች ከባድ ዋጋ እየከፈሉ ነው። ግጭቱ በሰው ሕይወት እና በንብረት ላይ ከሚያደርሰው ጉዳት ባሻገር በሴቶች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት እና ሰቆቃ ትኩረትን አላገኘም። ቢቢሲ ለወራት ባካሄደው ክትትል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሴቶች የመደፈር እና የወሲባዊ ጥቃት ሰለባ መሆናቸውን መረጃ አግኝቷል።
በብርሌ ፍቅር የወደቁት ፈረንጅ 'ብርሌ ውስጥ የኢትዮጵያ ታሪክ አለ' ይላሉ
ሰሞኑን አረቄ ብሔራዊ አጀንዳ ሆና የማኅበራዊ ሚዲያ አናት ላይ ወጥታ ነበር። ጠጅ ቢሆን አናት ላይ አይወጣም፤ ወደ ጉልበት ነው የሚወርደው። ጠጅ ለመጨረሻ ጊዜ ጉዳይ ሆኖ የሥነ መንግሥቱ አናት ላይ ወጥቶ፣ 'ብሔራዊ አጀንዳ' የነበረው በዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ዘመን ነው። ድሮ ጠጅ በብርሌ ይቀርብ ነበር። ከዚያ በብርሌ ይጠጣ ጀመር። ጠጅ ግን እንደ አረቄ ማንም ‘ተራ ዜጋ’ ብድግ አድርጎ አያንደቀድቀውም።ብርሌ ውስጥ የመደብ ታሪክ አለ። የዘመን ታሪክ አለ። የጭሰኛና የመሳፍንት ታሪክ አለ። ያልተሳከረ።
ዓለምን የሚዞረው ኢትዮጵያዊ ከዩቲዩብ ምን ያህል ያገኛል?
ከተከፈተ በዚህ ወር 20 ዓመት የሆነው የቪዲዮ ማጋሪያው የማኅበራዊ ሚዲያ መድረክ ዩቲዩብ ለብዙዎች የተለያዩ አጋጣሚዎችን ፈጥሯል። ከእነዚህም መካከል አቤል ብርሃኑ አንዱ ነው፤ በዩቲዩብ አማካኝነት 62 ሀገራትን ዟሯል። ያልረገጠው አህጉር አንታርቲካን ብቻ ነው። ሁሉንም የአሜሪካ ግዛቶች አካሏል። ከዘጠኝ ዓመታት በላይ ዩቲዩብ ላይ የቆየው አቤል ከዩቲዩብ ምንያህል ያገኛል?
ቪዲዮ, በአርሰናል ‘ፍቅር የወደቁት’ የ65 ዓመቷ እናት፡ ወይዘሮ እቴቱ ማሞ, ርዝመት 3,29
ከእንግሊዝ ታላላቅ ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነው የአርሰናል የልብ ደጋፊ የሆኑት ወ/ሮ እቴቱ ማሞ የ65 ዓመት እናት ናቸው። ላለፉት 20 ዓመታት አርሰናልን ያለማቋረጥ ደግፈዋል። እንደብዙዎቹ የቡድኑ ደጋፊዎች ዘንድሮ አርሰናል ዋንጫ ባለማንሳቱ ቢከፉም ድጋፋቸው ግን እንደሚቀጥል ይናገራሉ። ከሁሉም ተጫዋቾች ይልቅ እሳቸው ገብረኢየሱ ለሚሉት ለጋብሬል ጀሱስ እና ለቡካዮ ሳካ የተለየ ፍቅር አላቸው።
እነ ሞገስ አስገዶም፣ አብረሃ ደቦጭ፣ ፕ/ር አስራት ወልደየስ፣ ፕ/ር መስፍን ወ/ማሪያም፣ ስብሐት ገ/እግዚአብሔር የተማሩበት ተፈሪ መኰንን
ተፈሪ መኰንን ትምህርት ቤት ታሪክ የዘመናዊት ኢትዮጵያ ንድፍ እንደማለት ነው። ላለፉት 100 ዓመታት ታላላቅ ሰዎችን ወልዷል። ለመኾኑ ይህ ተማሪ ቤት እነማንን አፈራ? ይህ ሐተታ በ100 ዓመት ታሪኩ ውስጥ በአንድም ሆነ በሌላ አሻራቸውን ያሳረፉትን ግለሰቦች ያወሳል፤ ከካናዳዊያን ጄስዊቶች እስከ ከንቲባ አዳነች አበቤ፤ ከቱጃሩ ራስ ኃይሉ ተክለሃይማኖት እስከ ቢሊየነሩ ሼክ አላሙዲን፣ ከሐኪም ወርቅነህ እሸቴ እስከ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ።
ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት የምትገኘው አሊ ዶሮ እና አካባቢዋ ለምን የእገታ ማዕከል ሆኑ?
ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ በሕዝብ እና በጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እና እገታዎች ተበራክተዋል። ይህ ክስተት ደግሞ ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው የሰሜን ሸዋ አካባቢ በተደጋጋሚ ሲከሰት ቆይቷል። በተለይ አሊ ዶሮ የሚባለው ቦታ የጥቃት እና የእገታ ማዕከል ሆኗል እየተባለ ነው። ቢቢሲ በተለይ ይህ ቦታ ለምን የመንገደኞች እና የአሽከርካሪዎች ‘የሞት ቀጣና’ ሆነ? በሚል ለወራት የዘለቀ ምርመራ አድርጓል።
ባይተዋር ከተማ፡ “ፒያሳ፣ ካዛንቺስ... ሰፈሬ አልመስል አሉኝ”
ባለፉት ዓመታት በአዲስ አበባ በቅርስነት ተመዝግበው የነበሩ እንዲሁም ሌሎችም ታሪካዊ ሕንጻዎች፣ ቤቶች እና አካባቢዎች እንደ ዋዛ አፈር ለብሰዋል። በዚህ ዘገባ፣ አንድን ሕንጻ ወይም ቤት ቅርስ አልያም ታሪካዊ ሥፍራ ለማለት መስፈርቱ ምንድን ነው? የታሪካዊ ሕንጻዎች እና ቤቶች መፍረስ በታሪክ፣ በነዋሪዎች ሥነ ልቦና፣ በኪነ ሕንጻ እና በማኅበራዊ መስተጋብር ላይ ምን ጫና ያሳድራል? ቅርሶች እና ታሪካዊ ሥፍራዎችን እንዴት ጠብቆ ማደስ፣ ማዘመን፣ መልሰው አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ማድረግ እንዲሁም ከሌሎች ግንባታዎች ጋር ጎን ለጎን እንዲሄዱ ማድረግ ይቻላል? የሚሉት እና ተያያዥ ነጥቦች ተዳስሰዋል።
“ሰው መሃል ሆኜ ሁሉም ጨካኝ ሆኖብኝ ነበር” - የፀጋ በላቸው ዘጠኝ የጠለፋ ቀናት
ግንቦት 2015 ዓ.ም. የተፈጸመው የፀጋ በላቸው ጠለፋ ብዙዎችን ያስቆጣ፣ መነጋገሪያም የሆነ የወንጀል ድርጊት ነበር። ፀጋ፤ ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ በፊት ተጠልፋ ያሳለፈቻቸውን ቀናት በተመለከተ ለመጀመሪያ ጊዜ ለቢቢሲ በዝርዝር ተናግራለች። ከቢቢሲ ጋር በነበራት ዘለግ ያለ ቆይታ፤ ስለተጠለፈችበት መንገድ እና ስላሳለፈቻቸው ዘጠኝ ቀናት በዝርዝር ተርካለች። ከጠለፋው ነጻ የወጣችበት መንገድም አስቀድሞ በክልሉ መንግሥት ከተገለጸው የተለየ እንደሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ ተናግራለች። ለምን ከኢትዮጵያ እንደተሰደደች እና ስለ ቀጣይ ዕቅዶቿም እንዲሁ አጋርታለች።
". . . ከምድሩ ይልቅ የሰማዩን መንገድ ለመምረጥ ተገደናል" እገታ ያሰጋቸው መንገደኞች
ባለፉት ዓመታት በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ውስጥ የሚካሄዱ ግጭቶች እና በታጣቂዎች የሚፈጸሙ እገታዎች ዜጎች በፈለጉት ጊዜ እና መንገድ በአገሪቱ ውስጥ እንዳይንቀሳቀሱ ብርቱ ስጋት ፈጥሮባቸዋል። በተለይ ደግሞ የመንገደኞች ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎችን በማድረግ የሚፈጸሙት ያላባሩ እገታዎች በዋነኞቹ የአገሪቱ ክልሎች ውስጥ እንቅስቃሴን አዳጋች አድርገውታል። በዚህም ሳቢያ አቅሙ ያላቸው እና የግድ የሆነባቸው ሰዎች ፊታዎችን ወደ አየር ትራንስፖርት አዙረዋል።
"'ቁርጭምጭሚት' የሚለው ቃል ያስቀኛል'' ለ23 ዓመታት ለፈረንጆች አማርኛን ያስተማረችው ፖላንዳዊት፣ ዶ/ር ኤቫ ቮልክ-ሶሬ
ፓላንዳዊቷ ዶ/ር ኤቫን የአማርኛ ቋንቋን ከ40 ዓመት በፊት ተምራ በዲግሪ ከተመረቀች በኋላ ከሃያ ዓመታት በላይ በማስተማር በርካቶችን በአማርኛ ቋንቋ ዲግሪ አስይዛለች። የምታስተምርበት ዩኒቨርስቲ ወደ 80 ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ አማርኛን እያስተማረ ነው። አማርኛ ቋንቋን “ፏፏቴ ነው” የምትለው ዶ/ር ኤቫን በአገሯ በአማርኛ አስተርጓሚነት ትሠራለች። ለመሆኑ እንዴት ከአማርኛ ጋር ተዋወቀች?
"ብልጽግናዎች ይዘውን እንዲጠፉ አንፈቅድም፤ አገራችን ሕዝባችን ነው፤ ዝም አንላቸውም" - ጃዋር መሐመድ
በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ጉልህ ስፍራ ካላቸው ፖለቲከኞች መካከል ጃዋር መሃመድ አንዱ ነው። ለዓመታት ያህል በኦሮሚያ የነበሩ ትግሎችን እንዲሁም ተቃውሞዎችን ከጀርባም ሆነ ከፊት ሆኖ በማስተባበር እና በመምራት ግንባር ቀደም ነው።የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ አመራሩ ጃዋር ከትውልድ አንስቶ በፖለቲካ ህይወቱ የተጓዘበትን ህይወቱ ላይ የሚያጠነጥን 'አልጸጸትም' የተሰኘውን መጽሐፍ ታህሳስ 10/ 2017 ዓ.ም በኬንያዋ መዲና ናይሮቢ ያስመርቃል። ጃዋር መሃመድ በአገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ፣ በቀጣይ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ስለሚኖረው ሚና፣ አገሪቱ ስላለችበት ሁኔታ ከቢቢሲ አማርኛ ጋር ቆይታ አድርጓል።


